በጋራ ለመስራት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ

የካቲት፡2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ ለመስራት በሚያስላቸው የስራ ሂደቶች ዙሪያ የሁለትዮሽ ስምምነት አደረጉ፡፡
አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ መንግስታዊ ተቋም እንደመሆኑ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በአቅም ግንባታ በተከታታይ ትምህርት ፤በቴክኖሎጂ ሽግግር ፤በጥናትና ምርምር ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ጋራ ስምምነት ፈጥረዋል፡፡
ይህን ትብብር አስመልክተው በተለየዩ ደረጃ የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች በኮሌጁ ውስጥ ጉብኝት አድረገዋል፡፡ በጉብኝቱ በሁለቱ ተቋማት በጋራ ሊያሰሩ የሚችሉ የመስሪያ ቦታዎች፤ላብራቶሪ እና አጠቃላይ የኮሌጁን ገፅታ ተመልክተዋል፡፡
የሁለቱ ተቋማት የጋራ ትብብር የመግባቢያ ሰነድ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታረቀኝ ብርሃኑ እና የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ ፈርመዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት አቶ ግሩም እንደገለፁት ተግባረዕድ ኮሌጅ በሃገራችን አንጋፋ እና ለ8 አስርት አመታት በቴክኒካዊ እና ሙያ ዘርፍ ላይ በቂ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ በተለዩ የትብብር ዘርፎች ላይ አጋርነትን ለመመስረት ፈቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያዞ አቶ ግሩም ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተቋማዊ አቅም ግንባራ፤በተከታታይ ትምህርት ፤በምርምር እና የማማከር ስራዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩነቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታረቀኝ ብርሃኑ የሁለቱን ተቋማት ትብብር አስመልክተው እንደገለፁት በሁለቱ ተቋማት ውስጥ ለመማር ማስተማሪያ የሚሆን በቂ መሰረተ ልማት መኖሩን ጠቁመው ተቋማቱ ያላቸውን ሃብት በጋራ መጠቀም ያስቀመጡትን ራዕይ ለማሳካት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ ትብብራቸውን በማጠናከር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ በዋናነት በተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብር አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ በቅርቡ የሚሰጠውን ትምህርት በመደገፍ አስፈላጊ ግብዓቶችን እንደሚያሟላ ተገልጿል፡፡
ዘገባው የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *