የከተማ አቀፍ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና ዘመቻ

አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የቶም የህክምና መሳሪያዎች ተከላ እና ጥገና ድርጅት በጋራ በመሆን የሚያካሂዱት የከተማ አቀፍ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሐግብር ተከናወነ።

የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የቶም የህክምና መሳሪያዎች ተከላ እና ጥገና ድርጅት በጋራ በመሆን የሚያካሂዱት የከተማ አቀፍ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሐግብር ተከናወነ

መንግስት ባስቀመጠው የ Public Private Partnership Strategy (PPP) መሰረት ቀደም ሲል ሁለቱ ተቋማት MOU(Memorandum of Understanding) መፈራረማቸዉ ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሁለቱን ተቋማት ግኑኝነት ለማሳደግ እና ማህረሰቡን በጤናዉ ዘርፍ ለመደገፍ ይህ ዘመቻ በኮሌጃችን እንዲሁም በጤና ተቋማቱ በመገኘት ጥገና እንደሚካሔድ በመርሐግብሩ ተገልጿል።

አያይዘዉም የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ የመክፈቻ ስርዓቱ ላይ በኮሌጃችን በሚገኘዉ የባዮሜዲካል ስልጠና ዘርፍ በCovid ወረርሽኝ ወቅት በርከት ያሉ የጤና መሳሪያዎች እንደተጠገኑ አስታዉሰዉ አሁንም በሚደረገዉ ዘመቻ ላይ ላቅ ያለ አስተዋፆ በተቋማቱ እንደሚደረግ ገልፀዉ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመክፈቻ መርሐግብሩ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ አጥላባቸዉን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ እና ሞያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ጤና ቢሮ ተወካዮች ተገኝተዉ ለዘመቻዉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ እና ከዘመቻ ባሻገር የዕዉቀት ሽግግር እንደሚደረግበት ገልፀዋል።

የቶሚ ህክምና መሳሪያዎች ተከላ እና ጥገና ማዕከል ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ቶማስ ገብረመስቀል በበኩላቸዉ ለሀገራቸዉ ይህን የመሰለ ዘመቻ ላይ መሳተፍ እድለኝነት መሆኑን ገልፀዉ ለሚዲያ አካላት እና በዉጭ ሀገር ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን በዘርፉ እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨራሻም በክብር እንግዶች የጥገና ማዕከሉ ተመርቆ በይፋ ለሁለት ወራት የሚቆየዉ ዘመቻ ተጀምሯል።

አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

ሚያዚያ 16, 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *