ተግባረእድ ሚዲያ
የኮሌጃችን ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ አዲስ አበባ ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መሠርት በማድርግ በዉጤት የሚገለፁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው ብለዋል ።
የISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርዓት ለመተግበረ ከታህሳስ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ ኮሌጁን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ብሎም ከከተማ አስተዳደር እሴት እዉቅና ማግኘቱን ገልፀዋል ።
GIZ ከሚተገበርባቸው ፕሮጀክቶች የኢትዩጵያ እና የጀርመን ገቨርመንት የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ በGIZ በኩል KFW፣ STEEP ፣ sport for development አጠቃላይ ቲቬት ተቋማት የተሰሩ ስራዎች ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደ ማሳያነት የተመረጠ ሲሆን ለወደፊትም አብርው እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።
በመጨርሻም በኢንኩቤሽን ሴንተር ፣ በአውቶሞቲቭ ፣ ጋርመንትና ቴክስታይል የስልጠና ዘርፎች ጉብኝት አድርገዋል።
ተግባረእድ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት