Addis Ababa Tegbareid Polytechnic College Staff Participated in Entrepreneurial Training in Dire Dawa.

We are pleased to announce that a group of dedicated staff members from Addis Ababa Tegbareid Polytechnic College participated in an intensive Entrepreneurial Competency Training in Dire Dawa. This program, Powered by Cinop, Funded by European Union ,aimed at enhancing …

የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ክፍል በትብብር ስልጠና ከኮሌጁ ጋር ከሚሰሩ ኢንዱስትሪዎች ጋር የውይይት እና የምክክር መድረክ አካሔደ::The project coordination department of Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College held a Two Round dialogue and consultation forum with industries that work with the college through cooperative training.

በውይይት መድረኩ ላይ ሲኖፕ የተባለው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት እና ተባባሪዎቹ ከተግባረ ዕድ ጋር በጋራ በመሆን የትብብር ስልጠና ማጠናከር የሚል አላማ በመያዝ ፕሮጀክት እየተገበሩ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን በዛሬ የውይይት መድረክ በኮሌጁ እንዲሁም በኢንዱስትሪው በኩል ያሉ ተግዳሮቶች የመለየት እና መፍትሔያቸውን የማመላከት ውይይት …

በአዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲጂታል ተቋምን እውን ለማድረግ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው። The movement to realize a digital institution in Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College.

በዚህ እንቅስቃሴው 360⁰ VR video በመቅረፅ ለተማሪዎች ኢንተራክቲቭ የሆነ የትምህርት መርጃ ማዘጋጀት የሚያችል ስልጠና Cinop ከሚባል ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር መሰጠት ለማስጀመር ስልጠናዎች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ ። Trainings are being given in collaboration with an international organization called Cinop, …

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ የ GIZ country ዳይሬክተሮች በአዲስአበባ  ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አደርጉ ። GIZ country directors from different African countries exchanged experience and visited Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College.

ተግባረእድ ሚዲያ የኮሌጃችን ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ አዲስ አበባ ተግባረእድ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መሠርት በማድርግ  በዉጤት የሚገለፁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው ብለዋል ። የISO 9001:2015  የጥራት አመራር ስርዓት ለመተግበረ  ከታህሳስ 2016 …

የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ/ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ በዛሬው ዕለት ጀመረ። Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College 2017 Registration of current students started today.

አንጋፋው የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት 1150 ሰልጣኞችን አስመረቀ:: The elite Polytechnic College, Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College, graduated 1150 trainees today.

እንኳን ደስ አላችሁ ተግባረ ዕድ ሚዲያ 2016 አንጋፋው የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት 1150 ሰልጣኞችን አስመረቀ:: በመደበኛ መርሐግብር ከደረጃ 2-5 በ10 የስልጠና ዘርፍች የሰለጠኑ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል:: የዛሬው ተመራቂዎቻችን የኮሌጁን የምዘና ፈተና በሚገባ ማጠናቀቃቸው ልዩ …

ISO 9001: 2015 QMS ሰርተፍኬትን የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በይፋ ተረከበ። Addis Ababa Tegbare-Id Polytechnic College have Officially Received Certificate for QMS ISO 9001:2015 .

ተግባረ ዕድ ሚዲያ 2016 ዓ/ም

ISO 9001: 2015 QMS ሰርተፍኬትን የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በይፋ ተረከበ።

በአዲስ አበባ ስራ እና ክሕሎት ቢሮ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሰራር ስርዓትነት ሲተገብረው የቆየውን የISO 9001: 2015 QMS ሰርተፍኬትን በዛሬው ዕለት ከኢትዮጱያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከወ/ሮ መአዛ አበራ እጅ በዛሬው ዕለት በይፋ ሰርተፍኬቱን ተረክቧል።

ሰርተፍኬቱን የተረከቡት የኮሌጃችን ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ ” ISO 9001: 2015 QMS ከታሕሳስ ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በመተግበራችን የደንበኞቻችንን እርካታ ያማከለ አገልግሎት መስጠት እና ደንበኞችችን በአገልግሎታችን ያረኩበትን ምክንያት ነቅሰን አውጥተን የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዓለም አቀፍ እና ተገማች ስራዎችን እንድንሰራ አድርጎናል። ይሕንን የአሰራር ስርዓት እንዲተገበር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ለተወጣችሁ ለሁላችሁም የኮሌጁ ማኅበረሰብ አካላት ምስጋና ይገባችኋል” ብለው ለአይሶ ማስተባበሪያ ቡድን አባላት የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥተዋል።

የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የሆኑት ዶ/ር አበራ ብሩ (በአዲስ አበባ ስራ እና ክሕሎት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ) ”ISO 9001: 2015 ጥራት ያለው የአስተዳደር ስርዓትን በመተግበራችን 3 ዋና ዋና ጥቅሞች አሉት 1. ከስልጠና አንጻር የምናሰለጥናቸው ሰልጣኞች በዓለም ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ፤ 2. በተሟላ ደረጃ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እና ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ 3. በገበያ የሚፈለጉ የተለያዩ አገልግሎቶችን እና ምርቶችን በማቅረብ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርጋል” ያሉ ሲሆን አያይዘውም ”ሌሎች ኮሌጆች የጀመራችሁትን የትግበራ ሂደት አጠናቃችሁ ወደ እዚሕ ስርዓት በቅርቡ እንደምትቀላቀሉ ሙሉ እምነት አለኝ” ብለዋል።

ሰርተፍኬቱን ለኮሌጃችን ያስረከቡት ከኢትዮጱያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ከወ/ሮ መአዛ አበራ ”ኮሌጁን እንደ ሞዴል አድርገን እንወስደዋለን። ሌሎች ኮሌጆችም ከተግባረ ዕድ ልምድ በመውሰድ የአሰራር ስርዓቱን መተግበር ይኖርባችኋል” ብለው ተግባረ ዕድን ”በቀጣይ ሌሎች ዓለም ዓቀፍ ሰርተፍኬቶችን እንድትወስዱ ትጋታችሁ ይቀጥል” ብለው ሰርተፍኬቱን አስረክበዋል።

ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከታሕሳስ 12/2016 ዓ/ም ጀምሮ ISO 9001: 2015 ጥራት ያለው የአስተዳደር ስርዓትን እየተገበረ የሚገኝ የ82 ዓመት አንጋፋ እና ዘመናዊ ኮሌጅ ነው።

ተግባረ ዕድ ኮሚዩኒኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት