ኢትዮጲያ በዕደ ጥበብ ሙያዎች ቅርሶች የረጅም ጊዜ ታሪክ ቢኖራትም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳና ሳይሻሻሉ ና ለመህበራዊ ዕድገት የጎላ አስተዎጽኦ ሳያበረክቱ መቆየታቸው ነው፡፡ በያዝንው ምዕተ ዓመት መባቻ ላይ በአነስተኛ የጎጆ ኢንድስተሪ ዘርፍ በዘመናዊ ዘዴ ምርት የማምረት ስራ በመጀመሩ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ከባህላዊ የዕደ ጥበብ ሙያ /ክህሎት ማስተላለፊያ መንገድ የተሻለ ዘዴ ወይም መንገድ መቀየሻ አስፈላጊና ግዴታ እየሆነ መጣ፡፡ በዚህም መሰረት ሰራተኞች /አምራቾች ለመሳሪያ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብክነትን አሶግደው በቅልጥፍና እንዲያመርቱ ለማድረግ በስረዓት የተዘጋጀ ስልጠና ተጀመረ፡፡ በሀገራችን ከፋሽስት ጣሊያን ወረራ በኋላ አንዳንድ የማምረቻ ድርጅቶችን ለመማንቀሳቀስና አዳዲሶች ለማቋቋም የሰለጠነ ባለሙያ ማግኘት የግድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኙቱ የስልጠና ተቋማት ማስራት ጀመሩ፡፡ ከነዚህም አንዱና አንጋፋው የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ት/ቤት በ1934ዓም ሊቋቋም ችሉዋል፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ት/ቤት አንጋፋ የቴክኒክና የሙያ ት/ቤት ከተቋቋመበት ከ1934ዓም ጀምሮ የተለያዩ የእድገት ደረጃዎችን አሳልፉዋል፡፡ ይህ ት/ቤት ስራ እንደጀመረ የሚመራው በፈረንሳዊ ዳይሬክተር ስለነበረ ካአማሪኛ ጋር ፍረንሳይኛም የማስተማሪያ ቋንቋ ሆኖ የት/ቤቱም ስም ”Ecole National Des Arts et Techniques” የረቂቅ ትበብና የዕጅ ብለሐት ስራ ተማሪ ቤት በሚል ስም ይጠራ ነበረ፡፡ከ1934ዓም እስከ 1937ዓም በነበረው ጊዜ ሰልጣኞቹ የተለየ የትምህርት ደረጃ ሳያስፈልጋቸው ማንበብና መጻፍ የሚችሉ ወጣቶችን እየተቀበለ ግማሽ ቀን የልምምድ ስራ (practical instructions) ግማሽ ቀን ደግሞ ጅምናስቲክና ሰልፍ እንዲከታተሉ ይደረግ ነበር፡፡በወቅቱ የነበውን የባለሙያዎች አስፈላጊነት ለማመልከት ጽ/ቤቱ በጊዜው ዘሬውኑየሚል አላማ አንግቦ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ በዚህን ወቅት ኢትዮጲያዊያን መምህራን ማግኘት አስቸጋሪ ስለነበረ ስልጠናው በፈረንሳዮች፣ ጣሊያኖችና በአንድ ቤልጄማዊ ሲካሄድ ቆየ፡፡ በ1937ዓም የኢትዮጲያ መንግስት ከሲውድን መንግስተ ጋር ባደረገው የቴክኒክ የተtራዶ ስምምነት መሰረት የአዲስ አበባ ተግበረዕድ ት/ቤት በርካታ የትመህርት መስጫ መሳሪያዎች ለመግኘት ቻለ፡፡ቀስ በቀስም በተለይ በ1938ዓም እንግሊዘኛ ቋንቋ ፈረንሳይኛን ተካ፡፡ የስልጠናወ ጊዜም ከ3 ወራት ወደ 6 ወራት ተራዘሞ ከቀየ በኋላ በዚሁ ዓመት 3 ዓመት እንዲሆን ተደረገ፡፡የተምህር አሰጣጡም ተጠናክሮ ሙሉ ቀን እንዲሰጥ ሆነ፡፡ በ1942ዓም የስልጠናው ጊዜ 4 ዓመት እንዲሆን ከተደረገ መኋላ የሰልጣኞችን እድል ለማስፈት/ለማመቻቸት ሲባል ግማሽ ቀን በተለየዩ ድርጅቶች ውስጥ የልምምድ አገልግሎተ እንዲሰጡ ተደረገ፡፡ ይህ አሰራር እስከ 1949ዓም የቆየ ሲሆን በዚሁ ወቅት ተጨማሪ ህንጻዎች ተሰርተው የትምህርት ቤቱን የማሰልጠን አቅም በማጎልበት የሰልጣኞች ቁጥር እንዲጨምር ሆኑዋል፡፡ ከ1948 ዓም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ሚገቡ ሰልጣኞች 8ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያለፉ ሆኖ ሰልጠናውም እንደነበረው ለ4 ዓመታት (8+4) አንዲሆን ተደረገ፡፡ በዚህም የስልጠና ወቅት የመጀመሪያውን ዓመት ሁሉም ሰልጣኞች አንድ አይነት ትምሀርት እንዲከታተሉ ተደርጎ ከ2ተኛ ዓመት ጀምሮ ግን ለ3 ዓመታት በአንድ የሙያ መስክ ሲካሄድ የነበረው ሰልጠና አሰከ 1969ዓም ቆይቱዋል፡፡ ኮሌጁ የተለያዩ የዕድገት ደረጃዎችን በማለፍ ወደ ፖሊ ተክኒክ ኮሌጅነት ያደገ ሲሆን አንድ ዋና ዲን እና 3 ምክትል ዲኖችን የያዘ ነው፡ በአሁኑ ወቅት ኮሌጁ 3004 የቀን መደበኛ፣2148 የማታ ተመሪዎችና 243 የሳታላይት የድግሪ ተማሪዎች የያዘ ሲሆን በድምሩ 5395 የሚሆኑ ተማሪዎችን በ10 የትምህርት ክፈሎችና በ46 የትምሀርት ዘርፎች እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን 52 የሚሆኑ የተግባር መለማመጃ ሾቦችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ከዚህም በተጨማሪ 402 የሚሆኑ የድጋፍና የአስተዳደር ሰራተኞች አሉት፡፡

Addis Ababa Tegbareid Polytechnic college, established in 1942 G.C with the assistance of the Italian Government known as” Gonderan during that time “, it was the first pioneer “Technical School of the country “which provides necessary technicians and technical supervisors for different sectors such as Ethiopian airlines, electric and power authority, telecommunication, manufacturing industries agricultural industries in nationwide. AATPTC, have a legal personality as a poly technique college of the city government by law and regulations. Since then, the college was and still is providing vocational education mainly in the technical occupations (metal manufacturing, electricity, electronics, automotive but also in construction, woodwork, Textile, ICT) starting in 10+/2+3 programs and from 2006 in level I-V. The training in level V has currently started.