“ከ350ሺ ብር በላይ ወጪ ዳነ፡፡”
Newsየአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኑፋችቸሪንግ ስልጠና ዘርፍ በወርክሾፖቹ ውስጥ የሚገኙ የስልጠና እና የማምረቻ ማሽኖች የስልጠና ዘርፉ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች በጋራ በመሆን የተበላሹ ማሽኖችን በመጠገን መንግስት ሊያወጣ የሚችለውን ከ350ሺ ብር በላይ ወጪ አስቀርተው ማሽኖቹን ጠግነው ስራ አስጀምረዋል፡፡
አባት ብርሃኔ፣ ንጉስ ግርማ እና ተመስገን ያረጋል የተባሉ የተከበሩ አሰልጣኞች ከሰልጣኞች ጋር በመተባበር ማሽኖቹ የገጠማቸውን ችግር በሳንሳዊ ጥናት በመለየት ማሽኖቹን ሊጠግኑ ችለዋል፡፡ በተለይ ከ4 ዓመት በላይ ተበላሽቶ እና የተለያዩ ባለሙያዎች ሊጠግኑ ያልቻሉትን ሌዝ ማሽን (lathe machine) በመጠገን ስራ መጀመሩ አስመስጋኝ ተግባር ሆኗል፡፡
የኮሌጁ ኮር አመራር እና የተቋማት ልማት ማስተባበሪያ የስራ ክፍል በወርክሾፑ በመገኘት ለአሰልጣኞች እና ለሰልጣኞች ምስጋናን አቅርበዋል፡፡ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተስፋዬ አድማሱ “በሀገር ወዳድ ስሜት ይሕንን በማድረጋችሁ በኮሌጁ ስም እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡
አቶ ልኡልሰገድ ኃይሉ (የማኑፋክቸሪንግ ስልጠና ዘርፍ ተጠሪ) “እነዚሕን እና ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ጥገናዎችን በራስ አቅም በማከናወናችን የመንግስትን ወጪ ከመቀነስ በተጨማሪ የእውቀት ሽግግር በማድረግ የማሽኖቹን ስሪት በደንብ እየተረዳን እንገኛለን፡፡” ያሉ ሲሆን ጥገናዎቹ እንደሚቀጥሉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
“ተግባረ ዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን






