4 ዳይሬክቶሬቶች ሽግሽግ እና አዲስ ምደባ ተካሔደ::
ተግባረ ዕድ ሚዲያ መጋቢት 1/ 2017 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት 3 የዳይሬክቶሬቶች ሽግሽግ ሲያደርግ 1 አዲስ ዳይሬክቶሬት መድቧል::
በእዚሕም አቶ ኃ/ሥላሴ ገ/ሥላሴ የሰው ሐብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት: ወ/ሮ አስናቀች በዛብሕ የግዢ ዳይሬክቶሬት: አቶ ተሰማ ሳሙኤል የንብረት ዳይሬክቶሬት እና አቶ ፈይሳ ኢረና የውስጥ ኦዲት ዳይሬክተር በመሆን ተመድበዋል::
ለሁሉም ዳይሬክቶሬቶች መልካም የስራ ጊዜን እንመኛለን::
ተግባረ ዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን
