የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር /Ministry of Labour and Skill

በክብርት ወ/ሮ ነቢያ መሃመድ የስራ እና ክህሎት ሚኒስተር ዲኤታ የተመራው ልዑክ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የድጋፍና ክትትል መርሃግብር አከናወነ።

የልዑካን ቡድኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት፣ ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ፣ ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተወጣጣ ሲሆን በተቋሙ የተለያዩ ክፍሎች በመዘዋወር በተለይ የተቋም ግንባታ እና የፈሪፎርም ተግባራት አፈፃፀም ተገምግመዋል።

ከመስክ ምልከታው በዃላ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ በሁለቱ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ጠቅለል ያለ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ ሪፖርቱ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በምክትል ዲኖቹ አማካኝነት ማብራሪያና ምላሽ ተሰቶበታል።

ክብርት ሚኒስትር ዲዔታዋ በተለይ በተቋም ግንባታና ሪፎርም አፈፃፀም ላይ በኮሌጁ የታየው አበረታች ውጤት በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በተለይ የጥራት አመራር ስርዓቱን አፅንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀው፣ የዘርፉን ተልዕኮ በላቀ ከፍታ ለመፈፀም እንደ አዲስ አበባ ተግባረዕድ ያሉ አንጋፋ ተቋማት ተምሳሌታዊ ሚናቸው ከመወጣት ባሻገር ቀሪ የክህሎት ልማት ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አፅንኦት በመስጠት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።