ዪያንግ ቮኬሽናል እና ቴክኒካል ኮሌጅ
የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከቻይናው ዪያንግ ቮኬሽናል እና ቴክኒካል ከሚባል ኮሌጅ ጋር አብሮ የመስራት ውል ስምምነት የመፈራረም መርሃግብር በዛሬው እለት ተከናወነ፡፡
የቻይናው ኮሌጅ እና የተግባረ-ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች እና ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የፊርማ ስነ ስርዓቱ ተግባራዊ ሆኗል።
በእዚሕ ስምምነት መሰረት ተግባረ- ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከቻይናው ኮሌጅ በሰው ኃይል፣ በአሰራር እና ግብአ መልካም ተሞክሮዎችን እና ድጋፎችን የሚያገኝበት መልካም ዕድሎች ተፈጥረዋል። ከውል ስምምነቱ በተጨማሪ ልኡካኑን የኮሌጁን ወርክሾፖች እና የኢትዮጱያን ባሕል የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግል አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የመስግስትን ወጪ ቀንሶ ጥራት ያለው ስልጠና ለምስጠት እየተጋ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው፡፡
ተግባረ ዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ









